BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
በጋምቤላ ከተማ የሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ጥቃት እና ሁከት
በጋምቤላ ከተማ ባለፉት ጥቂት ቀናት በተፈፀሙ ጥቃቶች የሰዎች ሕይወት ማለፉን ነዋሪዎች እና የሆስፒታል ምንጮች ተናገሩ። በተደጋጋሚ በሚፈፀሙ ግጭቶች እና ጥቃቶች የምትታወቀው የጋምቤላ ከተማ ረቡዕ ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም. ከፍተኛ ሁከት እና አለመረጋጋት ሰፍኖባት እንዳሳለፈች እና ዛሬም የተኩስ ድምጾች መሰማታቸውን ሦስት የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ቀጥታ, ሁቲዎች በየመንን ፕሬዚዳንታዊ ቤተ-መንግሥት ላይ በፈጸሙት ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ
የሁቲ ታጣቂዎች በኤደን በሚገኘው ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ላይ በፈጸሙት የሚሳዔል ጥቃት አምስት ሰዎች መገደላቸውን እና 16 መቁሰላቸው ተገለፀ። የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር ሞአማር አል ኢራይኒ ለቢቢሲ አምስት ሚሳዔል መተኮሱን ገልጸው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሌሎች ሚኒስትሮች ምንም ጉዳት አልደረሰባቸውም ብለዋል።
ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋር በተያያዘ ባለፉት 5 ወራት አሜሪካ የወሰደቻቸው 5 እርምጃዎች
ደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት በፕሪቶሪያ ስምምነት አማካኝነት እንዲገታ ከፍተኛ ሚና ከነበራቸው አካላት መካከል የአፍሪካ ኅብረት እና አሜሪካ ይጠቀሳሉ። አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ዋነኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ምዕራባውያን አገራት አንዷ ናት። የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከሳምንታት በፊት ዳግም ሲቀሰቀስ ቀድመው መግለጫ ካወጡ አገራትም አንዷ ናት። አሜሪካ ከጦርነት መነሳት በፊት እና በኋላ የወሰደቻቸውን እርምጃዎች እንደሚከተለው ቃኝተናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮ ምን ተነጋገሩ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በስልክ ተወያይተዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ፤ ንግግራቸው ከኤርትራ ጋር "እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት" የተመለከተ መሆኑ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የውይይቱን ይዘት በዝርዝር ባይገልጹም "እጅግ ፍሬያማ" መሆኑን አስታውቀዋል።
'በሕይወት እንተርፋለን አላልንም' ፡ በህወሓት ቁጥጥር ስር የቆዩት የቀድሞ ባለሥልጣናት ምን ገጠማቸው?
የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ፣ አራት የቀድሞ ባለሥልጣናት ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ከነበሩበት እስር አምልጠው በኢትዮጵያ ሠራዊት እጅ ከገቡ በኋላ ወደ መቀለ መመለሳቸውን ተናግረዋል። ባለሥልጣናቱ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በቀድሞ ጓዶቻቸው ከየቤታቸው ታግተው ከተወሰዱ በኋላ ያሳለፉትን እና እንዴት ሊያመልጡ እንደቻሉ ከመካከላቸው አንዱ ለቢቢሲ አጋርተዋል።
ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ
አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ
ስለ ሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መንግሥት ለምን ዝምታን መረጠ? የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ?
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ሁለት ሳምንት አልፎታል፤ የፌደራሉ መንግሥት እና አጋር ኃይሉ መቀለን እና ሌሎች የትግራይ አካባቢዎችን ተቆጣጥረዋል። ከጦርነቱ ጅማሮ አንስቶ ተሳታፊ እንደሆኑ ሲነገር የነበረው የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በብዛት ወደ ትግራይ መግባታቸው ተዘግቧል። ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ ባድረጉት ንግግርም ሆነ መንግሥታቸው ስለ ጦርነቱ እስካሁን በይፋ ያሉት ያሉት ነገር የለም፤ ለምን?
ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከዲፕሎማሲ ውዝግብ እስከ ፀጥታው ምክር ቤት አቤቱታ እስካሁን የምናውቀው
ሁለት ሳምንት ያለፈው በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ጦርነት እንደቀጠለ ነው። በዚህ ሳምንት የጦርነቱ ዋነኛው ጉዳይ የኤርትራ ወታደሮች ከድንበር በሻገር በብዙ ኪሎ ሜትሮች ርቀው ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባታቸው ነው። ይህም ኢትዮጵያ ወረራ እንደተፈጸመባት በመግለጽ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ደብዳቤ እንድትጽፍ አድርጓታል። እስካሁን በተፈጠረው ቀውስ ዙሪያ ስላሉ ዋና ዋና ሁኔታዎች ምን እናውቃለን?
ትግራይ በኮማንድ ፖስት እንደምትመራ እና ከስድስት ወር በኋላ ምርጫ እንደሚካሄድ ተነገረ
የህወሓት መሪዎች መቀለን ጨምሮ ከበርካታ የትግራይ ከተሞች ለቅቀው ከወጡ በኋላ ክልሉ በፌደራል መንግሥቱ ኮማንድ ፖስት ሥር እንደሚቆይ እና በትግራይ ምርጫ እንደሚካሄድ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት እና በአሁኑ ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ይህንን የተናገሩት ቲቢኤስ ከተባለ መገናኛ ብዙኃን ጋር በትግርኛ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።
ለሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የመቀለ በረራ ዛሬ ሲጀመር የፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣናት ወደ ክልሉ ተጉዘዋል
ጦርነቱ ዳግም መቀስቀሱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሳምንታት አቋርጦት የነበረውን የመቀለ በረራ ዛሬ እሑድ ሲጀምር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣናት እና የትግራይ ሰላም ኃይሎች መሪዎች በመጀመሪያው ጉዞ ወደ መቀለ መግባታቸው ተዘግቧል።
ኤርትራ ለተመድ በላከችው ደብዳቤ "ኢትዮጵያ ራስን በመከላከል ስም ጦርነትን ምክንያታዊ ልታደርግ ነው" ስትል ከሰሰች
ኤርትራ ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በላከችው ደብዳቤ፤ ኢትዮጵያ "ራስን በመከላከል ስም" በሉዓላዊት የተመድ አባል ላይ የምትፈጽመውን ጦርነት ምክንያታዊ ለማድረግ እየሞከረች ነው ስትል ከሰሰች። በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ መስከረም 30/2019 ዓ. ም. በተጻፈው ደብዳቤ ላይ፣ የኢትዮጵያ "የማታለል ሙከራ ጭብጥ አልባ እና የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ የማገናዘብ አቅም የናቀ ነው" ስትል አሥመራ ወንጅላለች።
ኢትዮጵያ "ለተፈጸመባት ወረራ ራሷን ከመከላከል ውጪ አማራጭ እንደሌላት" ለተመድ የፀጥታ ምክር ቤት አባላት አሳወቀች
ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በደብዳቤ አሳወቀች። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት በጻፉት ደብዳቤ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን ገልጸዋል።
የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በብዛት መግባታቸውን የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ
የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀው መግባታቸውን እንደተመለከቱ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኤርትራ ወታደሮች በአዲግራት ከተማ በኩል ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች በጭነት ተሽከርካሪዎች እና በእግራቸው ሲያቋርጡ የተመለከቱት ከዛሬ ረቡዕ ማለዳ ጀምሮ መሆኑን ተናግረዋል።
"ድርቁ፣ ረሃቡ፣ መፈናቀሉ ሳይበቃ ወደ ሌላ ዙር ጦርነት እየገባን ይመስላል"- የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ መግባት ያሰጋቸው ነዋሪዎች
ኢትዮጵያ በኤርትራ "ወረራ እንደተፈጸመባት" አስታውቃ፣ የአሥመራ ወታደሮች አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ አሳስባለች። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአዲግራት እና እዳጋ ሐሙስ ነዋሪዎችም የኤርትራ ወታደሮችን እንደተመለከቱ እና ስጋት እንደገባቸው ገልጸዋል።
በአድዋ ከተማ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የእርዳታ ሠራተኞች ተናገሩ
በአድዋ በሚገኘው ሰገን ሆቴል እና አካባቢውን ዒላማ ባደረጉ አራት ዙር ጥቃቶች 11 ሰዎች ሲገደሉ በሆቴሉ እና ሌሎች የንግድ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዕለቱ ከሰገን ሆቴል በተጨማሪ ፓን አፍሪካን እና ሸዊት ሆቴሎችም ላይ በተመሳሳይ ጥቃት እንደደረሰባቸው የዓይን እማኞች ገልፀዋል። በተጨማሪም እሑድ ለሰኞ አጥቢያ በሽራሮ አካባቢ በሚገኝ የስደተኞች ካምፕ ላይ በተፈፀመ ሌላ ጥቃት ስምንት ሰዎች መገደላቸውን የእርዳታ ሠራተኞችን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
"በኢትዮጵያ ውስጥ እጁን ያስገባ ምላሹን በእጥፍ እንደሚያገኝ ጥርጥር የለውም"
የኤርትራ ሠራዊት ድንበር ተሻግሮ ባለፉት ቀናት በተካሄዱ ውጊያዎች ውስጥ መሳተፉን በመግለጽ የኢትዮጵያ ምላሽ ከባድ እንደሚሆን ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን ተናገሩ። ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት አብረሃም በላይ (ዶ/ር) የኤርትራ መንግሥት ጦር በጦርነቱ በቀጥታ መሣተፉን በመጥቀስ "እጁን እያስገባ የማያርፍ አካል ካለ ምላሹ ምን እንደሆነ በጣም ግልጽ ነው" ብለዋል።
የኢትዮ-ኤርትራ የዲፕሎማሲ ቁርሾ ባለፉት 36 ዓመታት
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ እንደገና የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን አቋርጠዋል። ይህ የቅርብ ጊዜ የዲፕሎማሲ ስብራት በሁለቱ አገራት መካከል ለአስርት ዓመታት የቆየውን ተለዋዋጭ ግንኙነት እንደገና ወደ ፊት አምጥቷል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ባለፉት 36 ዓመታት ውስጥ ከቅርብ ወዳጅነት እና ትብብር እስከ ጦርነት፣ ከዚያም ወደ ረዥም የዲፕሎማሲ መራራቅና "ጦርነትም ሰላምም የሌለበት" ሁኔታ የደረሱ ሲሆን፣ በኋላም ዕርቅና የግንኙነት መሻሻል አሳይተዋል።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, “እኛ አዲስ አገር ስለሆንን ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁ አይደለንም”
ለጋዜጠኞች ክፍት ወዳልሆነችው ኤርትራ በቅርቡ የመጓዝ ዕድል አግኝታ የነበረችው የሮይተርስ ዘጋቢ ጁሊያን ፓራቪሲኒ አሥመራ በጣሊያን ጊዜ የተገነቡ ሕንጻዎቿን ጠብቃ ብዙም እንቅስቃሴ የማይደረግባት ሆና አግኝታታለች። የኢንተርኔት አገልግሎት ቁጥጥር የሚደረግበት እና ውስን በመሆኑ ሕዝቡ ከቀሪው ዓለም መነጠሉንም ታዝባለች። የአገሪቱ ባለሥልጣናትም ኤርትራ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁ አይደለችም ብለዋታል።
ቪዲዮ, የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እና ከኤርትራ ጋር ያለው ውጥረት
በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ቀውስ የበለጠ ያወሳስባል ስለተባለው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እስካሁን ምን እናውቃለን? ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በቀጥታ ጦርነት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ?
ቪዲዮ, “ከትብብሩ ጀርባ ኤርትራ፣ ግብፅ እና ሱዳን አሉበት” ጃዋር መሐመድ
ሰባት የተቃዋሚ ኃይሎች የፈጠሩትን ትብብር አስመልክቶ ቢቢሲ ከፖለቲከኛው ጃዋር መሐመድ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። በቃለ መጠይቁ ትብብሩ ሦስት ውጤቶች ሊኖሩት እንደሚችሉ ተናግረዋል። ከዚህም ባለፈ ኤርትራ፣ ግብፅ እና ሱዳን ከትበብሩ ጀርባ እንዳሉ ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ሊያጠፋን ይችላል?
ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በተለያዩ ዘርፎች ላይ ውሎ ከፍተኛ ጥቅምን አስገኝቷል። በዚህም ውስብስብ ነገሮችን ከማቅለል አልፎ በርካታ ተግባራትን በቀላሉ ለመፈጸም አስችሏል። ይህ ደግሞ በተለያዩ መስኮች የሰዎችን ሥራ እየወሰደ እንደሆነ ሲገልጽ ቆይቶ አሁን ደግሞ የሰውን ልጅ ሊያጠፋ ይችላል የሚል ስጋት እየተሰማ ነው
ቪዲዮ, አነጋጋሪ የሆነው የቻይናው ፕሬዝዳንት የካይሮ ጉብኝት
የቻይናው ፕሬዝዳንት ካይሮን በጎበኙበት ወቅት ግብፅ በአባይ እና በቀይ ባሕር ላይ የምታራምዳቸውን አቋሞች የሚደግፍ የጋራ መግለጫ ሁለቱ አገራት አውጥተዋል። የዓለማችን አንዷ ኃያል አገር ቻይና ይህንን አቋም ማንጸባረቋ ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው?
ቪዲዮ, ግብፅ ትቀላቀለዋለች እየተባለ ያለው ቱርክ፣ ሳዑዲ እና ፓኪስታን የመሠረቱት 'የሙስሊም ኔቶ'
ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ፓኪስታን 'የመካ ስምምነት'ን ከፈረሙ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኗቸዋል። አንዳንድ ተንታኞች አገራቱ የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት "የሱኒ ስምምነት" ወይም "የሙስሊም ኔቶ" ሲሉ ጠርተውታል። አንዳንዶች እንደ ኢራን እና እስራኤል ላሉ አገራት የተላለፈ መልዕክት አድርገው አቅርበውታል። ሌሎች ደግሞ ይህ ስምምነት አገራቱ ለደኅንነት ዋስትና በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ለመቀነስ ያላቸውን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ነው ይላሉ። ነገር ግን ሙሉው ስምምነት ለሕዝብ ይፋ ባለመሆኑ እየተሰሙ ያሉት መላምቶች ብቻ ናቸው።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አነጋጋሪ ጉዳይ
የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታሪክ፣ አሠራር እና አወቃቀር
ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ መሠረት አዲሱ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መስከረም 25/2019 ዓ.ም. ሥራውን ይጀምራል። ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት በአገሪቱ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ የሚያሳልፈው ምክር ቤት ታሪክ ምን ይመስላል? የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አወቃቀር እና ሥራውን እንዴት እንደሚያከናውን ምን ያህል ያውቃሉ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዓመት ከ600 ቶን በላይ የከበሩ ማዕድናትን የማጣራት አቅም ያለው ፋብሪካ ሥራ ማስጀመራቸውን ተናገሩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዓመት ከ600 ቶን በላይ የከበሩ ማዕድናትን የማጣራት አቅም ያለው ፋብሪካ ሥራ አስጀመሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቅዳሜ መስከረም 30/2019 ዓ.ም. ሥራ ያስጀመሩት ይህ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ እስካሁን ድረስ ጥሬ ወርቅን ወደ ውጭ በመላክ ላይ ብቻ ተወስና ለቆየችው ኢትዮጵያ በዘርፉ ላይ ያለውን የእሴት መጨመር ችግር እንደሚቀርፈው ተናግረዋል። የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካው በአገር ውስጥ እና በቀጣናው የሚመረተው ወርቅ እሴት ታክሎበት በተሻለ ዋጋ ለገበያ ለማቅረብ ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥርም ጨምረው አብራርተዋል።
ትብብር የመሠረቱት ታጣቂ ቡድኖች አንድ የሚያደርጋቸው እና የሚያለያያቸው ምንድን ነው?
ሰባት ታጣቂ ቡድኖች "ትብብር ለኅልውና" የተሰኘ ጥምረት መመሥረታቸውን እሁድ መስከረም 10/2019 ዓ.ም. አስታውቀዋል። ይህንን ትብብር ከመሠረቱት የትጥቅ ቡድኖች መካከል የተወሰኑት በአንድ ወቅት በጠላትነት የሚተያዩ እና እርስ በርስ የተዋጉ ነበሩ። እነዚህ ትብብር መሥርተናል የሚሉት ታጣቂ ቡድኖች ባለፉት ዓመታት በጠላትነት የሚተያዩ አንዳንድ ጊዜም ግጭት ውስጥ የገቡ ነበሩ። ቡድኖቹን ምን አንድ ያደርጋቸዋል? በምንስ ይለያያሉ?
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ስለተቀሰቀሰው ግጭት እስካሁን የምናውቀው
የትግራይ የእርስ በርስ ጦርነት በፕሪቶርያ ስምምነት ከተገታ ወዲህ ከረቡዕ መስከረም 13 አንስቶ ግጭት በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግመኛ ተቀስቅሷል። ረቡዕ ዕለት ግጭቱ ስለ መጀመሩ ይፋዊ መረጃ ቢወጣም ማክሰኞ ዕለት በትግራይ አላማጣ ከተማ ተከታታይ የድሮን እና የአውሮፕላን ጥቃቶች መፈጸማቸው ተዘግቧል። ግጭቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የተለያዩ ወገኖች አቋማቸውን እያንጸባረቁ ነው። ስለ ግጭቱ አስካሁን የምናውቀው ምንድን ነው?
በሰሜን ኢትዮጵያ በፌደራል ኃይሎች እና በትግራይ ታጣቂዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ
ለወራት በውጥረት ውስጥ በቆየው የትግራይ ክልል ውስጥ ግጭት መቀስቀሱን የህወሓት እና የፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣናት ገለጹ። በትግራይ ኃይሎች እና በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት መካከል ጦርነት መቀስቀሱ የተገለጸው ረቡዕ መስከረም 13/2019 ዓ. ም. ማለዳ የትግራይ ኃይሎች መቀለ የሚገኘውን አውሮፕላን ማረፊያ ተቆጣጥረው በረራዎች መቋረጣቸው ከተነገረ በኋላ ነው።
የትግራይ ኃይሎች የመቀለ አውሮፕላን ማረፊያን "መቆጣጠራቸው" ከተሰማ በኋላ ወደ ክልሉ የሚደረጉ በረራዎች ተቋረጡ
የትግራይ ኃይሎች ዛሬ ማለዳ በክልሉ ዋና ከተማ መቀለ የሚገኘውን አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያን መቆጣጠራቸው ከተሰማ በኋላ ወደ ትግራይ በረራዎች ተቋረጡ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ረቡዕ ረፋድ ላይ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል የሚያደርገውን በረራ "ለጊዜው መቋረጡን" አስታውቋል።
ባለፉት 30 ዓመታት በኢትዮጵያ የተፈጠሩ ተጠቃሽ አምስት የፖለቲካ ጥምረቶች ከምን ደረሱ?
ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ በርካታ ኃይሎች በአንድ የሚያስተሳስሯቸውን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ትስስሮችን ፈጥረው ተንቀሳቅሰዋል። ከእነዚህም መካከል አገሪቱን በአዲስ መልክ ያዋቀረው እና ለረዥም ጊዜ ያስተዳደረው ኢሕአዴግ እና ከተቃዋሚዎች መካከል የበርካቶችን ድጋፍ አግኝቶ የነበረው ቅንጅት ተጠቃሾች ናቸው። እነዚህ እና ሌሎች ባለፉት አሥርታት የታዩ ስብስቦች ለምን ተመሠረቱ? ምንስ አስገኙ? ፍጻሜያቸውስ ምን ሆነ?
ጥምረት መመሥረታቸውን ስላስታወቁት ታጣቂ ቡድኖች ምን እናውቃለን?
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራውን መንግሥት ከሥልጣን ማስወገድ ዓላማው ያደረገ ነው የተበላው "ትብብር ለኅልውና" የተሰኘ ጥምረት መመሥረቱ ይፋ ሆኗል። ይህ ስብስብ በኢትዮጵያ የብሔር ፖለቲካ ውስጥ አንጋፋ ከሆኑት ጀምሮ ዓመታት የሚቆጠር ታሪክ ያላቸው ቡድኖች፣ እንዲሁም በጠላትነት ይተያዩ የነበሩ ቡድኖች ያሉበት ነው። በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሊ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች ውስጥ መሠረታቸውን ያደረጉት እነዚህ ታጣቂ ቡድኖች ታሪካዊ ዳራ ምን ይመስላል?
ስለትብብሩ እና ስለ ቀጣይ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ታዋቂዎቹ ፖለቲከኞች ጃዋር እና ልደቱ ምን ይላሉ?
አቶ ልደቱ አያሌው እና አቶ ጃዋር መሐመድ በሰባት ታጣቂ ኃይሎች የተመሠረተውን ፀረ-መንግሥት ትብብር በተመለከተ የተለያየ አቋም አላቸው። ሁለቱም ፖለቲከኞች የትብብሩን ምሥረታ አስፈላጊነት በተለያየ አገላለፅ ቢያምኑበትም በሂደቱ፣ በትብብሩ አባላት የእርስ በርስ ግንኙነት እና በቀጣይ ውጤቱ ላይ ግን ልዩነቶችን አንፀባርቀዋል። ቢቢሲ ሁለቱን ፖለቲከኞች ትብብሩን በተመለከተ አስተያየታቸውን እንዲሰጡት ጠይቋል የጠይቋቸዋል።
ከየፈርጁ
በአዲስ አበባ ተማሪዎችን ከፍተኛ ክፍያ ከሚጠይቁት ትምህርት ቤቶች መካከል ሦስቱ
በአዲስ አበባ የሚገኙ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ተማሪ በዓመት ከሚያስከፍሉት ክፍያ አንጻር ከፍተኛ የሚባሉ ዋጋዎችን ያስቀምጣሉ። በአውሮፓውያኑ 2026/27 የትምህርት ዘመን የወጡ የክፍያ መረጃዎች እነዚህ ትምህርት ቤቶች በዓመት እስከ 37 ሺህ ዶላር በላይ ወይም ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጋ ብር እንደሚያስከፍሉ ያመለክታሉ። ትምህርት ቤቶቹ እንደ ተማሪው ዜግነት፣ የክፍል ደረጃ እና የክፍያ ዓይነት የተለያየ ተመንም አላቸው።
ሙዚቃ በሱቅ፣ በወጥ ቤት፣ በወፍጮ ቤት፣ በጋራዥ. . . የሚያጫውቱት ዲጄዎች
ዲጄ ሲባል መጀመሪያ የሚመጣልን ምሥል ምናልባትም የዳንስ ወለል ላይ ወዝ ወዝ የሚሉ ሰዎች እና ብልጭ ድርግም የሚል መብራት ይሆናል። እነዚህ ዲጄዎች ግን ማንኛውንም ቦታ ለሙዚቃቸው መዳረሻ ማድረግ የሚችሉ ናቸው። ጋራዥ፣ ቴአትር ቤት፣ ፀጉር ቤት፣ መጻሕፍት መደብር፣ ልብስ ሰፊ ቤት፣ ግንባታው ያልተጠናቀቀ 40/60፣ ሸክላ ሠሪ ቤት፣ ወፍጮ ቤት፣ ውይይት ታክሲ. . . የማይገቡበት የለም።
አጃኢብ!
እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚወጣባቸው ግዙፍ የሽምግልና አበባዎች ፡ የአበባ አብዮት ወይስ የባህል ለውጥ?
ከጋብቻ በፊት የሚደረገው የሽምግልና ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ድግስ እና ገንዘብ የሚፈስበት እየሆነ መጥቷል። ከሚዘጋጀው ድል ያለ ድግስ ባሻገር በመቶ ሺዎች ብር የሚያስወጡ ቄንጠኛ ግዙፍ የአበባ ‘እቅፎች’ ደግሞ የሽምግልናው ሥርዓት አካል ሆነዋል። በተለይ የሚቀርበው የአበባ ስጦታ መነጋገሪያ ሆኗል። የሽምግልና ሥነ ሥርዓት የሰርግን ቦታ እየተካ ነው? ግዙፉ የአበባ ስጦታስ ከየት የመጣ ልማድ ነው?
የተመለሱ ጥያቄዎች
የአዲስ ዓመት አከባበር ሥርዓቶች በተለያዩ የዓለም አገራት
በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ አገራት ሕዝቦች አዲስ ዓመታቸውን የሚያከብሩት በተለያየ ጊዜ ነው። በርካታ የምዕራባውያን እና ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው አገራት ጥር ወር ላይ አዲስ ዓመታቸውን የሚጀምሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የእስያ አገራት ደግሞ ከዚህ የተለየ የአዲስ ዓመት አከባበር አላቸው። በተለያዩ የዓለማችን ክፍል የሚገኙ አገራት አዲስ ኣመትን እንዴት ያከብሩታል?
ቪዲዮ, ባለፓስፖርቶቹ የሰውን በሽታ የሚለዩት አይጦች, ርዝመት 1,28
ባለፓስፖርቶቹ የሰውን በሽታ የሚለዩት አይጦች
ቪዲዮ, የቦዲ ቢዩልደሮችን ልብ ቀጥ እያደረገ ያለው ነገር ምንድን ነው?, ርዝመት 1,24
የቦዲ ቢዩልደሮችን ልብ ቀጥ እያደረገ ያለው ነገር ምንድን ነው?















































































































