ቀጥታ, የአሜሪካ እና የኢራን የመጀመሪያ ዙር ድርድር ‘አበረታች ውጤት’ እንዳሳየ ተገለጸ

የአሜሪካ እና የኢራን የመጀመሪያ ዙር ድርድር “አበረታች ውጤት” እንዳሳየ አሸማጋዮቹ ኳታር እና ፓኪስታን አስታወቁ። ድርድሩ ትናንት እሑድ በስዊትዘርላንድ ተጀምሯል። ኳታር እና ፓኪስታን ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ “ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ኮሚቴ በ60 ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ላይ ተስማምቷል” ብለዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የአሜሪካ እና የኢራን የመጀመሪያ ዙር ድርድር 'አበረታች ውጤት' እንዳሳየ ተገለጸ

የቀጥታ ሽፋን

የአሜሪካ እና የኢራን የመጀመሪያ ዙር ድርድር ‘አበረታች ውጤት’ እንዳሳየ ተገለጸ

የአሜሪካ ልዑካን

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የአሜሪካ እና የኢራን የመጀመሪያ ዙር ድርድር “አበረታች ውጤት” እንዳሳየ አሸማጋዮቹ ኳታር እና ፓኪስታን አስታወቁ።

ድርድሩ ትናንት እሑድ በስዊትዘርላንድ ተጀምሯል። ሁለቱ አገራት ከስምምነት ላይ የደረሱት ባለፈው ሳምንት እንደነበር ይታወሳል።

ኳታር እና ፓኪስታን ዛሬ ሰኞ በጋራ ባወጡት መግለጫ “ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ኮሚቴ በ60 ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ላይ ተስማምቷል” ብለዋል።

በያዝነው ሳምንት የቴክኒክ ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት እንደሚቀጥል በመግለጫው ተመልክቷል።

በድርድሩ ተሳታፊ የሆኑ የአሜሪካ ዲፕሎማት እንደተናገሩት ውይይቱ “ከኢራን የወጡ አወዛጋቢ መልዕክቶችን ማጥራት ላይ ያተኮረ ነው”።

በተጨማሪም በሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነትን ማስተግበር እና የሆርሙዝ ወሽመጥን ማስከፈት የውይይቱ ግቦች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ተደራዳሪዎች

የፎቶው ባለመብት, Reuters